DJIBOUTI
|
|
FRONT FOR THE RESTORATION OF UNITY AND DEMOCRACY -FRUD- Frud_djibouti@hotmail.com የጅቡቲ የአንድነትና ዴሞክራሲ ማረጋገጫ ግንባር (ፍሩድ) ጋዜጣዊ መግለጫ የጅቡቲ መሪ የአካባቢው እሳት ለኳሽ ሆኗል ከዲሰምበር 23 ጀምሮ ኢትዮጵያ አፋር አካባቢ በሶማኢ ኢሳና በአፋርሮች መህል በተከሰተው ግጭት ሕይወታቸው ላለፈው ቤትሰቦች ፍሩድ ከልብ የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ጽናቱን ይስጣችሁ ይላል። ክልል ሁለት በሚል በሚጠራው የአፋር አካባቢና በጅቡቲም ቢሆን በአፋር ኢሳና አረቦች መሃከል በጎጥ ልዩነትን እያራገበ የግጭትን እሳት የለኮሰው የኦማር ገሌህ አገዛዝ ከተመሰረተብት ከ1997 ዓ፣ም. ጀምሮ የጎሳ መንግሥት መሆኑን አረጋግጧል ። ብሄራዊ መንግስት መሆን ያቃተው ይህ አገዛዝ ከጎሳና ጎጥ ፖለቲክና ይዘት ሊወጣም አለመቻሉን አሳይቷል ። ላለፉት አራት ወራት የጅቡቲ ዋና መሪዎች በግልጽ በአፋርና ኢሳዎች መሃል በኢትዮጵያ ግጭት ሊቀሰቅሱ ሲጥሩ አይተናል ።ይህም በዲሴምበር 23 በኡንዳ ጋዳማይቱና በአዳይቱ አካባቢዎች ፈንድቷል ። በአፋር አዲስ አመራር ከተመሰረተ ከጥቂት ቀናት በኋላ ይህ ግጭት መፈጠሩ በድንገት አይደለም ።በመቶዎች ሰዎች ሞተዋል።ቀደም በኢሳና አፋር መሃል ግጭትየግጦሽና መሰል ችግሮችን/ምክንያቶችን የትመለከተ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ግን ግጭቶቹ በኢትዮጵያ አገዛዞችና በተለይም በጅቡቲ አገዛዝ የፖለቲካና የስትራተጂ ምክንያቶች መሆኑ ይታወቃል ። ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በአሊ ሳቤህ.በነሓሴ ስብሰባ ካደረገ በኋላ ፕሬዚዳንት ኦማር ጋሌህ የውጥረት ዕቅድ በመተለም የኢትዮጵያ ኢሳዎችን ለመርዳት ወስኖ ተነስቷል ።በመጪው 2021 ዓ.ም. ለአምስተኛ ጊዜ ሊመረጥ ያቀደው ገሌህ የኢሳዎችን ድጋፍ ከመፈለጉ ባሻገር በአቢይ አህመድም ላይ ጫና ማድረግ ይፈልጋል ። ውስጠ አዋቂዎች እንደሚሉት የኦማር ገሌህ ዕቅድ ለኢትዮጵያ የሚያገለግሉትን ሶስት መንገዶችና ሃዲዶች ለመቆጣጠር ነው። ማለትም የባቡሩን ሃዲድ፤የገላፊና ጋሊሌ መንገድ። ወደነዚህ አካባቢዎች--የገልፊ አዲስ አበአን መንገድ ለመቆጣተር በርካታ ወታድሮችን ሲልክ ከባድ መሣሪያ ሳይቀር ማጉጓዙም ተዘግቧል ። ኢህ ወንጀለኛና ሀላፊነት የጎደለው ድርጊቱ ይፍትናው ገሌህ ጅቡቲና ማለትም አፋር ኢሳውና አረቡን ሊመራ አለመአሉን ግልጽ አድርጓል ። አገዛዙ በሕዝብ ላይ ፍጅትን ካክሄደ በኋላ · በተደጋጋሚ በዲኪል አፋሮች ላይ፤በባሪስሌ፤ዮቦኪ፤ኦቦክ፤ራንዳ ፤ዴይ፤ በተለይም አርሂባ በሶማሌዎች ላይ፤ጋዳቡርሲዎችና ኦሮሞዎች ላይ ላይ፤ · በሶማሊ ኢሳዎች ላይ በባልባላ፤በዮኒስ ሙሳና ቡልድሁቆ፤ · የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም የኢትዮፕያ አፋሮችና ኢአዎችን እንደ ጭዳ መጠቀም፤ ይህ አገዛዝ አዲስ ዕድገትና ብልጽግና አምጪን አመራር ፈላግፊ ጅቡቲን ለማስተዳደር ችሎታ ቢስ መሆኑን አረጋጧል ። የገሌህ መንግስት ወደ ውድቀቱ እያመራ ሊንኮታኮት የደረሰ ነው ። ይህ በኦማር ገለኤህ እየተፋመና እየተግፋ ያለው የስ በርስ ጦርነት ተገልብጦ የኦማር ገሌህን አገዛዝ ፍጻሜ ሊያመጣ የሚችልም ነው ። ለዚህም ነው ፍሩድ ግንባር ሁሉም የፖለቲካ ሀይሎች፤የሲቪል ማህበራት፤ ወዘተ በጋራ ቆመው ጅቡቲን ከአጥፊው አገዛዝ እንዲከላከሉ ጥሪ የሚያደርገው። በኢትዮጵያ ያሉም አፋሮችና ኢሳዎች ዩህን አጥፊ የርስ በርስ ጦርነት አቁመው የጅቡጢ አገዣዥ ባላስገባ መንገድ ተደራድረው ጭግሮቹን እንዲፈቱም ያሳስባቸዋል ። ብሩሰልስ፤ቤልጂም .27/12/2018 መሓመድ ካዳሚ Mohamed Kadamy ፍሩድ ፕሬዚዳንት ...
0 Comments
Leave a Reply. |
Archives
October 2022
Categories
All
|